Understanding Factors Affecting the Performance of Agricultural Extension System in Ethiopia

Abstract

አህፅሮት ይህ የምርምር ጽሁፍ የአገራችንን የግብርና ስርፀት አሁን ያለበትን ብቃትና አፈጻጸም እንዲሁም ለግብርና ስርፀቱ ዋና ዋና ማነቆ የሆኑ ምክንያቶችን በመለየት ይተነትናል፡፡ ምንጃር ሸንኮራና አደአ ወረዳ የጥናቱ መነሻ በማድረግ በግብርና ስርፀቱ ዋና ፈጻሜ የሆኑትን 143 የልማት ጣቢያ ሰራተኞችንና ሱፐርቫይዘሮችን በወካይነት አካቷል፡፡ በተጨማሪም ይህ ጥናት በግብርና ስርጸት ውስጥ በቂ ልምድ ካካበቱ ተመራማሪዎች፣ የልማት ጣቢያ ሰራተኞችና አርሶ አደሮች መረጃ አካቷል፡፡ ይህ ጥናት እንደሚያሳየው ምንም እንኳን መንግስት የግብርና ስርጸቱ ለሁሉም ተጠቃሚዎች በበቂ ሁኔታ እንዲደርስ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየሰራ ያለ ከመሆንም በተጨማሪ ከፍተኛ የሆነ የልማት ጣቢያ ሰራተኞችን ያሰለጠነና በማሰልጠን ላይ ቢሆንም፤ የግብርና ልማቱ በሚፈለገው ደረጃ ሊያድግ አልቻለም፡፡ ስለሆነም የግብርና ስርጸቱን አንቆ የያዙትን ማነቆዎች መፍታት ተገቢ እንደሆነ ይታመናል፡፡ የጥናት ውጤቱ እንደሚያሳየው በልማቱ ውስጥ ያሉ ዋና ዋና አካላትና አጋሮች ግንኙነትና ጥምረት ደካማ መሆን፣ የገበሬ ማሰልጠኛ ማዕከላት አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶች አለመሟላት፣ የልማት ጣቢያ ሰራተኞች በቅርበት ለገበሬው ተደራሽ ለመሆን የትራንስፖርት ችግር፣ የልማት ጣቢያ ሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት በሚፈለገው ደረጃ አለማደግና የአቅም ውስንነት፣ የልማት ጣቢያ ሰራተኞች ከዕቅድ እስከ ግምገማ ባለው ሂደት ተሳትፎ ውስን መሆን እና ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ አለመኖር ዋና ዋና ማነቆዎች መሆናቸው ተለይቷል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ይህ ጥናት ከመንግስት ቁርጠኝነትና ከሰው ሃይል ልማቱ ጎን ለጎን የልማት ጣቢያ ሰራተኞች የስራ ከባቢ ምቹ ማድረግና ለስራው የሚያስፈልጉ ግብዓቶችን በሚፈለገው ጊዜና መጠን መቅረብ እንደሚገባው ይጠቁማል፡፡ በመሆኑም የግብርና ስርጸት ማነቆዎችን በመፍታት የወደፊቱን ልማት ማፋጠን እንደሚቻል ጥናቱ ጠቁሟል፡፡  Abstract  This study is assessing the performance of the agricultural extension system and identifying factors explaining it. The paper used both quantitative and qualitative data collection methods. Quantitative data gathered based on a questionnaire survey of 143 development agents (DAs) in Minjar Shenkora and Ada’a districts. Qualitative data were collected from 25 key informants and eight separate focus group discussants. Quantitative data was analyzed by both descriptive statistics and econometric model while qualitative data were analyzed through categorization, narration and interpretation. Results show that, despite huge government investments and having one of the highest DA-to farmers’ ratio, Ethiopia has not been able to achieve the desired goals of agricultural advancement. This is mainly because of weak and limited interactions, synergies and partnership among actors, lack of adequate facilities of FTCs, lack of physical resources for mobility, DAs lack of work motivation, lack of strong supervision, lack of technical competence of DAs, and lack of involvement of DAs in the decision making process. The Econometric model results reveal that systems of rewards and sanctions, enforcement of performance targets, interaction and partnership among relevant actors, supervision, donor funding, number of motorbikes, and DAs capacity building trainings are most significantly influenced the performance of agricultural extension service. This research showed that number of DAs is not a sufficient condition of enhancing extension performance, but an effective extension system needs to focus on the enabling environment for DAs to be motivated to work as mandated

    Similar works